‎የሀገራት እድገት በፈጠራ አቅማቸው ይለካል — አቶ በዛብህ ገበየሁ

‎​ወላይታ ሶዶ:- ግንቦት 17/2018 ዓ.ም

‎​”ፈጠራና ቴክኖሎጂ ለሀገር ልማትና ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል፣ በፈጠራና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ልማትን በማፋጠን ሀገራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ያለመ ታላቅ የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን በወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በይፋ ተከፍቷል። ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው ደማቅ ኤግዚቢሽን ላይ በክላስተሩ ስር የሚገኙት የአረካ፣ የገሱባ፣ የበሌ፣ የጠበላ እና የሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች ያበለጸጓቸውን፣ ችግር ፈቺ የሆኑ የፈጠራ ሥራዎችና የምርምር ውጤቶች ለሕዝብ እይታ አቅርበዋል።

‎​

‎የሀገራት እድገት በፈጠራ አቅማቸው ይለካል” — አቶ በዛብህ ገበየሁ ​በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ኃላፊ አቶ በዛብህ ገበየሁ እንደገለጹት፤ የሀገራት ውድድር እና እድገት በፈጠራና በቴክኖሎጂ አቅም እንደሚለካ ጠቁመው፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በክህሎት የበለፀጉ ችግር ፈቺ ዜጎችን በማፍራት ረገድ የጎላ ኃላፊነት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

‎​የኤግዚቢሽኑ ዋና ዓላማ የፈጠራ ባለቤቶችን ማበረታታት፣ የተፈጠሩ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሀብት መቀየር እና ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ ውጤቶችን ማስፋፋት እንደሆነም ኃላፊው አብራርተዋል። በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ልዩ ትኩረት እየተሰጠ መሆኑን ያነሱት አቶ በዛብህ፣ በተለይም በኢንዱስትሪ፣ በግብርና፣ በቱሪዝም፣ በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ በጋርመንትና ሌዘር ዘርፎች ላይ የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን የማፍለቅና የማስፋፋት ሥራ በስፋት እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

‎​የፈጠራ ስራዎችን ከመማሪያ ክፍል ወደ ገበያ እያወጣን ነው — ኢንጅነር ያዕቆብ ያሲን ​የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን በከተማዋና በአካባቢው የሚስተዋሉ የማህበረሰቡን ችግሮች የሚቀረፉ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸው፤ የሠልጣኞችና የመምህራን ፈጠራዎች ከመማሪያ ክፍል ባሻገር ወደ ምርትና ገበያ እንዲገቡ ተቋሙ በትኩረት እየሠራ መሆኑን አስታውቀዋል። ​የዚህ ማሳያ ይሆን ዘንድ፦

‎​🚗 የኮሌጁ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ማዕከል እና

‎​🍞 የዳቦ ማምረቻና ማከፋፈያ ማዕከል በይፋ ሥራ መጀመራቸውንና ምርቶቻቸውንም ለማህበረሰቡ በሽያጭ ማቅረብ መጀመራቸውን አብስረዋል። ​ተቋሙ የሚሰጠው ስልጠና ሙሉ በሙሉ በክህሎት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን በማድረግ፣ ሰልጣኞች በተግባር አምርተው በመሸጥ ገቢ እንዲያገኙ እና ከስልጠና በኋላ ራሳቸውን ችለው ወደ ሥራ ዓለም እንዲገቡ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩንም ዋና ዲኑ አክለው ገልጸዋል።

‎​🛠️ በኤግዚቢሽኑ ምን ምን ቀረበ?

‎​ለቀጣዩች 3 ቀናት ክፍት ሆኖ በሚቆየው በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ፦

‎​⚙️ ለኢንዱስትሪ ድጋፍ የሚያደርጉ ማሽኖች፣

‎​🚜 ለእርሻ ሥራ የሚያግዙ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች፣

‎​🌿 ለአካባቢ ጥበቃ እና ለኃይል አጠቃቀም የተቀየሱ አዳዲስ ፈጠራዎች፣

‎​💡 ለማህበረሰቡ የዕለት ተዕለት ችግሮች ተግባራዊ መፍትሄ የሚሰጡ በርካታ ውጤቶች ለዕይታ ቀርበዋል።

‎​የአካባቢያችን ማህበረሰብ፣ የኢንዱስትሪ ባለቤቶችና ሠልጣኞች በመገኘት የወጣቶቻችንንና የቴክኒክና ሙያ ተቋማቶቻችንን አስደናቂ የፈጠራ አቅም እንዲመለከቱ ተጋብዘዋል።

‎የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

‎ጥራት ያለው ስልጠና ለተግባራዊ እውቀት!

‎​ለፈጣን እና ታማኝ መረጃዎች የገጻችን ቤተሰብ ይሁኑ!

‎ገጻችንን Like እና Follow ያድርጉ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *